Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home News Latest News የተቀናጀ የማህበረሰብ ልማት ፕሮግራም ለመተግበር አውደ ጥናት ተካሄደ

                          የተቀናጀ የማህበረሰብ ልማት ፕሮግራም ለመተግበር አውደ ጥናት ተካሄደ

                           meeting in libokemkem1

በአመልድና አልማ የተቀናጀ የማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክት የምክክር አውደ ጥናት ከአጋር አካላት ጋር በአዲስ ዘመን ከተማ ጥር 13/2011 . ተካሄደ፡፡

በአመልድ የተቀናጀ የማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክት ግሊመር ኦፍ ሆፕ ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ 151 ሚሊየን ብር ለሚቀጥሉት 4 ዓመታት (.. ከጥር 2019- 2023) በሊቦከምከም ወረዳ በተመረጡ 9 ቀበሌዎች የተቀናጅ የማህበረሰብ ልማት ስራ ይሰራል፡፡ 

                           meeting in libokemkem2

አውደጥናቱን የከፈቱት የአመልድ //ዳሬክተር አቶ ደጀኔ ምንልኩ፣ አመልድ ባለፉት 35 ዓመታት ውስጥ ከተለያዩ ረጂ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት በአማራ ክልል በድህነት ውስጥ ያሉ ዜጎችን ህይዎት ለመለወጥ ብዙ ስራ ስርቷል፤ የአሁኑ ፕሮጅክትም ተመሳሳይ ግብ አለው ብለዋል፡፡

የግሊመር ኦፍ ሆፕ ድርጅት በኢጥዮጵያ የኦፕሬሽን ዳሬክተር አቶ ካህሳይ ግርማይ፣ ግሊመር ኦፍ ሆፕ በኢትዮጵያ ለማህበረሰብ ልማት ከሚንቀሳቀስባቸው 4 ክልሎች (አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ እና ትግራይ ክልል) አንዱ የአማራ ክልል በመሆኑ ላለፉት 14 ዓመታት ብዙ የማህበረሰብ የልማት ስራዎችን መሰራቱን ተናግረው፤ በሊቦከምከም ወረዳ 9 የገጠር ቀበሌዎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ፣ የአካባቢና የግል ንፅህና ልማት ስራዎች ከአመልድ ጋር በቅንጅት ለመስራት ተስማምተን እየደገፍን ነው ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በወረዳው ለተመረጡ 9 ቀበሌዎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ለማቅረብ 69 የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ ፕሮከክቶችን (48 መካከለኛ ጥልቅ ጉድጓድ፣ 18 የእጅ ጉድጓድ እና ሌሎቸ ምንጭ ማጎልበት) ለመስራት አቅዷል፡፡ እንዲሁም የአካባቢውን ምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እና የአርሶ አደሩን ግብርና ስራ ለማቀላጠፍ 4 የመስኖ አውታሮች እና 3 የእንስሳት ጤና ክሊኒኮችን ይገነባሉ፡፡ 

የአርሶአደሮችን ቁጣባ ባህል ለማሳደግና የገንዘብ ምንጭ ለመፍጠር 5,000 አርሶ አደሮችን የሚያቅፍ 250 የመንደር ብድርና ቁጠባ ቡድን በማደራጀት እና ገንዘብ ቆጥበው ብድር እንዲያገኙ ለማድረግ ስልጠና የመስጠትና ሌሎች ተያያዥ ስራዎች ለመስራት ታዷል፡፡ በቁጠባ ቡድኖች በኩል ለአባላቶቹ ብድር አገልግሎት የሚውል 43,102,410 ብር በበፕሮጅክቱ መዘጋጀቱን እና ቀሪው 18,682,190 ብር ደግሞ በርብ ቁጠባና ብድር ዩኔን .የተ.የግ. እንደሚቀርብ በምክክር አውደ ጥናቱ ላይ ተገልጿል፡፡

 
Language Selection
Social Media
FacebookTwitter
Visitor Counter
Today8
Week134
All75069

Currently are 17 guests online


Poll
What do you think about our site?