አመልድ 6ኛው የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ውድድር ተሸላሚ ሆነ

                                  award

የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት በየዓመቱ ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶችን በማወዳደር ለሽልማት ያበቃሉ፡፡ ጥር 2 ቀን 2011 . በተካሄደው የጥራት ሽልማት ውድድር አመልድ 1 ደረጃ የዋንጫና የሰርቲፊኬት ተሸላሚ ሆኗል፡፡

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ክብርት / ሳህለወርቅ ዘውዴ በብሔራዊ ቤተ-መንግስት ሽልማቱን ሲሰጡ

ድርጅቱ ዘለቄታ ባላቸው የአካባቢና ደን ልማት ስራዎቹ፣ በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ቴክኖሎጅዎችንና አሰራሮችን መተግበሩ እንዲሁም የመስኖ ልማት አውታሮችን በመዘርጋት በአጠቃላይ በየዓመቱ 1.2 የሚጠጋ ገንዘብ በማንቀሳቀስ 1.5 ሚሊዮን ህዝብ ተደራሽ በማድረጉ ነው ለዚህ ሽልማት የበቃው ብለዋል ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ደጀኔ ምንልኩ፡፡

                                    award1

ከዚህ በተጨማሪ ድርጅቱ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚያስችሉ አሰራሮችን በማላመድ፣ የገበያ ትስስር በመፍጠር፣ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት የክልሉን ልማት እየደገፈ ይገኛል፡፡

አመልድ የተሻሻሉ የሰብልና የእንስሳት ዝርያዎችን በአርሶ አደሩ ቀየ በማድረስ፣ የእናቶችና የህጻናት ስርዓተ ምግብ እንዲሻሻል፣ ስራ የሌላቸው ወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር እንዲሁም ሴቶችና የአካል ጉዳተኞች የኢኮኖሚው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው፡፡

ድርጅቱ በሚያከናውናቸው የልማት ስኬቶች የውጭና የአገር ውስጥ ሽልማቶችን እያገኘ ባለበት በዚህ ሰዓት ከምንጊዜውም በተሻለ የልማት ስራዎችን በጋራ ለመስራት ለዓለም አቀፍና አገር አቀፍ ድርጅቶች ጥሪውን ያቀርባል፡፡

እንኳን ደስ ያላችሁ!