Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Content on this page requires a newer version of Adobe Flash Player.

Get Adobe Flash player

Home News Latest News የ2016 ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2017 ዕቅድ ትውውቅ ተካሄደ

2016 ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና 2017 ዕቅድ ትውውቅ ተካሄደ

በአማራ ክልል በሚከናወኑ ዘርፈ-ብዙ የልማት ስራዎች ጉልህ አሻራ ያለው ህዝባዊ የልማት ተቋም ነው፤ አመልድ፡፡ ድርጅቱ 2016 ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና 2017 ዕቅድ ትውውቅ ከሚያዝያ 2-4/2009 . በባህር ዳር ግራንድ ሪሶርትና ስፓ አካሂዷል፡፡

                               2016 meeting

ድርጅቱ 11ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ በድምቀት ባከበረበት ወቅት ቀርቦ የጸደቀው ያለፉት 3 ዓመታት (2014-2016) ሪፖርት ለሰራተኛው የቀረበ ሲሆን የአመልድ ጠቅላላ ጉባኤ ያፀደቃቸውን ዕቅዶች፤ የሥራ አመራር ቦርዱ በየጊዜው በዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ወቅት ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች ከወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር በማጣጣምና የልማት ሀብት በማፈላለግ የልማት ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል፡፡

በተለይም ደግሞ .. 2016 ድርጅቱ ወደ ከፍተኛ የዕድገት ምዕራፍ የተሸጋገረበት የስኬት አመት ነበር፡፡ ይህ ዓመት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ የኘሮጀክት ማስፈፀሚያ በጀት የተገኘበት የሶሻልA ኢንተርኘራይዝ የማቋቋም ተግባር የተጀመረበት እና አመልድ በአገር-አቀፍና በዓለም-አቀፍ ደረጃ ሽልማትና ዕውቅና ያገኘበት ዓመት ነበር፡፡


                            2016 meeting 1 

ሪፖርቱ የቁልፍና አበይት ተግባራት አፈጻጸም እንዲሁም የሶሻል ኢንተርፕራዝ ልማት አፈፃፀም በዝርዝር ቀርቧል፡፡ 2016 ውጭ ኦዲተር የፋይናንስ ህጋዊነት ምርመራእንከን የለሽ (Unqualified)” ውጤት የተገኘ ሲሆን ይህም የድርጅቱን የፋይናንስ አስተዳደር ጥንካሬ ያመለክታል፡፡

ከዚህ ባሻገር አመልድ በክልሉ መንግስት ሊሰፉ የሚችሉ ምርጥ ተሞክሮዎች ያሉት ሲሆን

  • የማህበረሰብ አቀፍ ደን ልማት (Community Based Greening Programe)
  • ተሳትፏዊ የደን አስተዳደር (Participatory Forest management)
  • ሁሉን አቀፍ የመሬት አያያዝና አስተዳደር አሰራር (Comprehensive Land Husbandry Approach)
  • የሃብት (የኑሮ) ደረጃን መሰረት ያደረገ የተጠቃሚ ልየታና ድጋፍ
  • በፀሐይ ሃይል የሚሰራ አምፖል (solar lantern)
  • ቤተሰብና በማህበረሰብ ደረጃ የዉሃ ማቆር ኩሬዎችን (household and community ponds) ማስፋፋት
  • ማህበረሰብ አቀፍ የመጠጥ ወሃና ስነ-ንጽህና ፕሮጀክት (Community managed Project)
  • በቤተሰብ ደረጃ የስርዓተ-ጾታ ትንተና (Gender Household Analysis) ማካሄድ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

አመልድ 2017 ዕቅድ በዝርዝር የቀረበ ሲሆን ተሳታፊዎች ጥያቄዎችንና ዕቅዱ እንዲዳብር የሚረዱ አስተያየቶችን ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችና አቅጣጫዎች የንቅናቄ ዕቅድ ቀርቦ ለተፈጻሚነቱ ሁሉም ርብርብ እንደሚያደርግ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

 

 

የአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ) ለክልሉና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ለ2011 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያለ፡- 
---------------------------------------------------------------

         newyear
በክልላችን ስትራቴጅያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የአጭርና የረጅም ጊዜ ፕሮግራሞችንና ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ የመንግስትንና የህዝቡን የልማት ክፍተቶች በመሙላት ትርጉም ያለው የልማት ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

ድርጅቱ በአካባቢና ደን ልማት፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ቴክኖሎጅዎችንና አሰራሮችን እንዲሁም የመስኖ ልማት አውታሮችን በመዘርጋት ጉልህ አስተዋጽኦ ሲያበረክት ቆይቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚያስችሉ አሰራሮችን በማላመድ፣ የገበያ ትስስር በመፍጠር፣ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት የክልሉን ልማት እየደገፈ ይገኛል፡፡

አመልድ የተሻሻሉ የሰብልና የእንስሳት ዝርያዎችን በአርሶ አደሩ ቀየ በማድረስ፣ የእናቶችና የህጻናት ስርዓተ ምግብ እንዲሻሻል፣ ስራ የሌላቸው ወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር እንዲሁም ሴቶችና የአካል ጉዳተኞች

የኢኮኖሚው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

ድርጅቱ በሚያከናውናቸው የልማት ስኬቶች የውጭና የአገር ውስጥ ሽልማቶችን ያገኘ ሲሆን ከምንጊዜውም በተሻለ የልማት ስራዎችን በጋራ ለመስራት ለዓለም አቀፍና አገር አቀፍ ድርጅቶች ጥሪውን ያቀርባል፡፡

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የብልጽግና እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡ 
የአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ)
--------------------------------------------------------
HAPPY ETHIOPIAN NEW YEAR- 2011 E.C.

 

 

We have got awarded "THE AMERICAN BIZZ 2017" prize for our outperforming accomplishments in program (Business) Excellence


ORDA’s Executive Director Acceptance Speech 


ORDA awarded globally the ESQR’s Quality Choice Prize 2016!

       

Organization for Rehabilitation & Development in Amhara (ORDA) is awarded 1st level trophy in the fourth Ethiopian Quality Award (EQA)

      

Language Selection
Social Media
FacebookTwitter
Visitor Counter
Today0
Week0
All66345

Currently are 12 guests online


Poll
What do you think about our site?